← All news
News Oct 20, 2026 · 18d ago

የጎንዮሽ ማቆሚያ ጭንቀትን የሚያስቀር የቻይናውያን ድንቅ የቴክኖሎጂ ፈጠራ

መኪናን በሁለት ተሽከርካሪዎች መካከል የጎንዮሽ ማቆም (Parallel Parking) ለብዙ አሽከርካሪዎች፣ በተለይም ጥበብ ለሚጠይቁ የከተማ መንገዶች፣ ትልቅ የመንዳት ፈተና እና ጭንቀት እንደሆነ ይታወቃል። ይህን የዘወተር ችግር በጥበብ ለማቃለል ያለመ አዲስ ቴክኖሎጂ በቻይናው የአውቶሞቢል አምራች ቸሪ አማካኝነት ይፋ ሆኗል። ኩባንያው ባካሄደው የቴክኖሎጂ ጉባኤ ላይ "ፌይዩ ኢንቴሊጀንት ድራይቪንግ" (Feiyu Intelligent Driving) የተሰኘውን ዘመናዊ የመንዳት እና የመሪ ስርዓት አስተዋውቋል።   በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሰፊ ትኩረትን እና አድናቆትን ባተረፈው በዚህ ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው፣ መኪናው ጎማዎቹን ወደ ጎን በማዞር በቀጥታ ወደ ጎን በመንሸራተት ወደ ማቆሚያው ስፍራ በሰከንዶች ውስጥ ይገባል። ይህም አሽከርካሪዎች መኪናቸውን ለማቆም ሲሉ ወደፊትና ወደኋላ እያመላለሱ የሚያባክኑትን ጊዜ፣ ጉልበትና የትራፊክ መጨናነቅ ሙሉ በሙሉ ያስቀረዋል።   የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓቶችን በማጣመር፣ የሰዎችን የዕለት ተዕለት ህይወት እና የመንዳት ልምድ የሚያቃልሉ አዳዲስ ፈጠራዎችን ለአለም ማቅረባቸውን አፋጥነው ቀጥለውበታል።