← All news
News Oct 20, 2026 · 18d ago

ሀሰተኛ መረጃ‼️

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መረጃ ነው። ​የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ተሹመዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የቆየው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀና ሀሰተኛ መረጃ ነው።