← All news
News Oct 18, 2026 · 21d ago

የኢቦላ ቫይረስ በኬንያ መከሰቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከፍተኛየቅድመ ዝግጅትና የቁጥጥር እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረች

የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ቀደም ሲል በኡጋንዳ እና በአሁኑ ወቅት በጎረቤት ኬንያ መከሰቱን ተከትሎ፣  የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI)፣ ከክልል ጤና ቢሮዎችና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር በሽታው ወደ ሀገር እንዳይገባና ከተከሰተም በፍጥነት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታወቀ። በዚህም መሠረት በአየርና በየብስ መግቢያና መውጫ በሮች ላይ የ24 ሰዓት የጤና ቅኝትና ቁጥጥር እየተካሄደ ሲሆን፤ የላቦራቶሪ ምርመራ አቅምን የማጠናከር፣ የልየታና ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድኖችን የማደራጀት፣ እንዲሁም ወረርሽኙ ከተከሰተባቸው ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ መንገደኞች ልዩ ክትትል የማድረግ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ሚኒስቴሩ ሕብረተሰቡ በበሽታው ዙሪያ የሚሰጡ ይፋዊ መረጃዎችን እንዲከታተል ያሰሰበ ሲሆን፤ ከወረርሽኙ ቀጠና የመጡ ወይም ከተጋላጭ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች ላይ ትኩሳት፣ የጡንቻ ሕመም፣ ማስታወክ ወይም ያልተለመደ የደም መፍሰስ ምልክቶች ከታዩ ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ ወይም በ 8335 እና 952 ነፃ የጥሪ መስመሮች ደውለው እንዲያሳውቁ ጥሪ አቅርቧል።