"ተታለው የህወሓት ጦርን ለተቀላቀሉ
አባላት የማሰቢያ ጊዜ ሰጥተናል" የትግራይ ሰላም ኃይል ከፌደራል መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን «ፅንፈኛ» ባለው የህወሓት ሠራዊት ላይ በወሰደው የጸረ ማጥቃት እርምጃ የኃይል ሚዛኑ ሙሉ በሙሉ መዛባቱን የሰላም ኃይሉ ቃል አቀባይ ኮለኔል ሰሎሞን ሃይለማሪያም ገለጹ። ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ፣ ሠራዊቱን ካዳከሙ በኋላ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ የነበረበት ቢሆንም፤ ተታለው ወይም አምነው የህወሓት ጦርን የተቀላቀሉ አባላት የማሰቢያ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል። «ቀንደኛ የፅንፈኛ ቡድኑ አባላት ወደ ኤርትራ ተሻግረዋል» ያሉት ኮለኔል ሰሎሞን፣ ከዚህ የተረፉ የሠራዊቱ አባላትና አመራሮች ግን አሁንም በትግራይ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በመሆኑም እነዚህ አካላት በተዘጋጁላቸው የመልሶ ማቋቋሚያ ቦታዎች ቀርበው የዕድሉ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።