← All news
News Oct 17, 2026 ¡ 21d ago

🚨 «ጌታቸው ረዳ ጄኔራል አል-ቡርሃን ለኢትዮጵያ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚያቀብሏቸው አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ለሱዳን ሕዝብ ምንም ፋይዳ እንደማይሰጡ ተቹ»

​የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ከቻይናው ሲጂቲኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በቀጣናዊ ደኅንነት እና ጂኦፖለቲካዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ​የጄኔራል አል-ቡርሃን ድጋፍ መተቸት፦ የሱዳኑ ሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚያቀብሏቸው አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ለሱዳን ሕዝብ የሚሰጡት ምንም ዓይነት ጥቅም እንደሌለ ጌታቸው ረዳ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ​የኤርትራና ግብፅ ጣልቃ ገብነት ማክሸፍ፦ የኤርትራ፣ የግብፅ እና የሱዳን ኃይሎች የሚከተሉት አጥፊ የጠብ አጫሪና የጣልቃ ገብነት ጎዳና መክሸፉን የገለጹት አማካሪው፤ ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ በጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት መሆኑን አስገንዝበዋል። ጦርነቱም በፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የተቀናበረ መሆኑን ጠቁመዋል። ​የትግራይ ክልል የቀጣይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዕቅድ፦ ክልሉ በሚቀጥሉት 6 ወራት በፌዴራል መንግሥቱ ሥር ሆኖ በባለአደራ አስተዳደር እንደሚመራ፣ ከዚህ ጊዜ በኋላም አጠቃላይ ነፃ ምርጫ ተካሂዶ አሸናፊው አካል የሥልጣን መንበር እንደሚረከብ አብራርተዋል።