ትራምፕ አዲሷን የዋይትሃውስ ቃል አቀባይ በተሾሙ በቀናት ውስጥ ከኃላፊነት አነሷቸው።
ኬቲ ዘካሪያ ኃላፊነቱን ለመወጣት የአቅም ችግር አለባት በማለት ነው ከስልጣን የተነሳችው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቃል አቀባይዋ ቻይናን በተመለከተ የምታራምደውን አቋም እንዳልወደዱትም ተገልጿል። ሰኞ እለት የተሾመችው ዛካሪያ ማክሰኞ የመጀመሪያውን መግለጫ ከሰጠች በኋላ አርብ ተባራለች። በኃላፊነት መቆየት የቻለችው አምስት ቀን ብቻ ነው።