ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ በግዙፍ ኢኮኖሚ ለአምስት ዓመታት ይዛው የቆየችውን የአንደኝነት ደረጃ ለኬንያ አስረከበች።
የኢትዮጵያ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ዋጋ 126 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የኬንያ ግን ወደ 135 ቢሊዮን ከፍ ማለቱን የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሪፖርት ያመለክታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ በግዙፍ ኢኮኖሚ ደረጃ ከ7ኛ ወደ 8ኛ ደረጃ ዝቅ ስትል፣ ኬንያ ባንጻሩ ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች። ኢትዮጵያ የቀዳሚነት ደረጃዋን ለማስረከቧ ዋናው ምክንያት የምርት ማነስ ሳይኾን፣ የብር ምንዛሬ ዋጋ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ከዶላር አንጻር ማሽቆልቆሉ እንደኾነ ተገልጧል። ከዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት አንጻር፣ ኢትዮጵያ አሁንም በኬንያ ላይ ከፍተኛ ብልጫ አላት።