በትግራይ ክልል የተደረገው ጦርነት ዋነኛው ኢንጂነር ኢሳይያስ አፈወርቂ ነው-አቶ ጌታቸው ረዳ‼️
አቶ ጌታቸው ረዳ ከሲጂቲኤን ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ በትግራይ ክልል የተደረገው ጦርነት በኢሳይያስ አፈወርቂ የተሳሳተ ስሌት መሆኑን ገልፀዋል። ኤርትራ ይህንን ያደረገችው እራሷን ለመከላከል እና ጦርነቱ ከኤርትራ ድንበር ለማራቅ በማሰብ እንደሆነ ገልፀዋል። ይህ የኢሳይያስ አፈወርቂ የተሳሳተ ስሌት መሆኑን ገልፀዋል። የግብፅ እና የሱዳንን ጣልቃ ገብነት በተመለከተ ግብጽ ኤርትራን እያስታጠቀች ቢሆንም የማይቆመውን ነገር ማስቆም አትችልም ብለዋል። ሱዳንም ለህወሓት የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን ማስታጠቁን ገልፀዋል።