የቦንብ ጥቃት ተፈፅሟል‼️
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ፣በወልዲያ እንዲሁም በማዕከላዊ ጎንደር፣በደቡብ ጎንደርየተለያዩ ከተሞች ላይ ለመከላከያ ሰራዊት አጋርነታቸውን ለማሳየት በዛሬው ዕለት የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል። ይህንን ተከትሎ በቆቦ ከተማ በነበረው ሰልፍ ላይ 3:20 አካባቢ የቦንብ ጥቃት ተፈፅሟል። በሰልፈኞች ላይ የደረሰው ጉዳት አልታወቀም። ከዚህ በተጨማሪ በመርሳ ከተማ አራት ጊዜ ሞርተር ተተኩሶ ሁለት ሰዎች ቆስለዋል።