← All news
News Oct 17, 2026 · 22d ago

አርትስ ቲቪ ስርጭቱን አቋረጠ

አርትስ ቲቪ ወርልድ (Arts TV World) ከሳተላይት እና ከዲጂታል ስርጭት ውጭ መሆኑ ኢትዮ ታይምስ ዘግቧል ። ጣቢያው በጋዜጠኛ አማረ አረጋዊ፣ በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በአትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያምና በሌሎች ባለሀብቶች የተመሠረተ ነው። የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያት ላይ የባለአክሲዮኖች አስተዳደራዊ ውዝግብና ሌሎች ጉዳዮች እየተጠቀሱ ቢሆንም፣ እስካሁን ከተቋሙም ሆነ ከሚዲያ ባለሥልጣኑ ይፋዊ ማብራሪያ አልተሰጠም።