← All news
News Oct 16, 2026 · 22d ago

10 ሚሊየን ብር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያን አክሲዮን መግዛት ይችላሉ

ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች በዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ አክሲዮን ግዢ ላይ ለመሳተፍ መኪናቸውንና ቤታቸውን ሳይጨምር ቢያንስ 10 ሚሊዮን ብር ሀብት ሊኖራቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አስታውቋል። አዲስ አበባ ላይ በተዘጋጀው የባለሀብቶች መድረክ ይፋ እንደተደረገው፣እያንዳንዱ አክሲዮን 74 ብር ከ90 ሳንቲም ዋጋ የወጣለት ሲሆን፣ ሽያጩም እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ይሁን እንጂ ይህ ዕድል ለሁሉም ክፍት የተደረገ ሳይሆን፣ ከ100 ለማይበልጡ ብቁ ባለሀብቶችና ተቋማት ብቻ የተወሰነ ነው። በናይጄሪያ የሚገኘውና በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፤ የነዳጅ ማጣራት አቅሙን በእጥፍ ለማሳደግ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ይህንን አክሲዮን ይፋ አድርጓል። ፋብሪካው በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ ብቻ 13 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እና 1 ነጥብ 78 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱ ተገልጿል።