'መኪኖቻችሁን ከከተማዋ ጎዳናዎች ይዛችሁ ውጡ!'
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ለአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። 'ለአንድ ዓመት ተኩል መክረናል፣ አስጠንቅቀናል፤ ከእንግዲህ ግን እርምጃ እንወስዳለን' ብሏል። ከመጠን በላይ በካይ ጭስ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች ሁለት አማራጭ ተሰጥቷቸዋል፦ የበካይ ጋዝ መቀነሻ ቴክኖሎጂ መግጠም፣ አለበለዚያ የከተማዋን ጎዳናዎች ለቀው መውጣት! ኃላፊዎቹ 'እስካሁን በጭስ ምክንያት ያቆምነው መኪና የለም፤ ከእንግዲህ ግን ይህ አይቀጥልም ሲሉ የመጨረሻውን ቀይ መስመር አስቀምጠዋል። በከተማዋ ለሚታየው የአየር ብክለት 32 በመቶው የተሽከርካሪዎች ጭስ ነው ተብሏል። ያረጁ መኪኖችና ታክሲዎች መንገዱን ለቀው ከወጡ የከተማዋ የትራንስፖርት እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል?