← All news
News Oct 16, 2026 · 22d ago

ዓይናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎችን ድጋሚ ማየት የሚያስችል ድንቅ ቴክኖሎጂ ተበሰረ!

የቴክኖሎጂው ቢሊየነር ኢሎን መስክ ለበርካታ ሰዎች አዲስ ተስፋ የሚያንፀባርቅ አስደናቂ ዜና ይዞ ብቅ ብሏል። ተቋሙ ኒውራሊንክ የዓይን ብርሃናቸውን በሙሉ ያጡ ሰዎችን ድጋሚ ማየት የሚያስችሉ ልዩ የአእምሮ ቺፖችን ለመትከል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል። ይህ ድንቅ የቴክኖሎጂ ግኝት የተጎዱትን የዓይን ክፍሎች በሙሉ በመዝለል፣ የእይታ መረጃዎችን በቀጥታ ወደ አእምሮአችን የእይታ ማዕከል ማስተላለፍ የሚችል ነው። ኢሎን መስክ እንደተናገረው ከሆነ ከመጪዎቹ 6 እስከ 12 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያዎቹን የእይታ ተከላዎች በሰዎች ላይ መሞከር ይጀምራሉ። ነገሩ በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም፤ በረጅም ጊዜ ሂደት ቴክኖሎጂው ከተራ የሰው ልጅ የተፈጥሮ እይታ አልፎ እንደ ኢንፍራሬድ እና አልትራቫዮሌት ያሉ ለሰው ልጅ ዓይን የማይታዩ ረቂቅ የብርሃን ሞገዶችን በከፍተኛ ጥራት ማየት የሚያስችል አቅም እንደሚያስኝም ገልጿል።