ተሿሚዎች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገቡ‼️
በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተሾሙ አዳዲስ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ለመውሰድ ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸው ተሰማ። ይህ ያልተለመደ እርምጃ የመጀመሪያው ዙር ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ባለስልጣናት በተከታታይ ተመሳሳይ ወታደራዊ ስልጠና እንደሚወስዱ ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በፓርላማ እና በተለያዩ መድረኮች ላይ፣ የመንግስት ሹመኞች "ቦርጭ ማውጣት እና ከመጠን በላይ መወፈር እንደሌለባቸው" በማንሳት፣ ጂም በመግባት እና ስፖርት በመስራት ንቁና ቀልጣፋ መሆን እንዳለባቸው በሳቅ የታጀበ ማሳሰቢያ ሲሰጡ ተሰምተው ነበር። Via:- ዘሐበሻ