← All news
News Oct 15, 2026 · 23d ago

ቡርኪና ፋሶ የቁንጅና ውድድሮችን አገደች

የምእራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ​ቡርኪና ፋሶ የወጣት ሴቶችን ዕውቀት እና ተሰጥኦ ለማክበር ሲባል የቁንጅና ውድድሮችን በማገድ በምትኩ የሳይንስ ውድድርን ይፋ አድርጋለች። በሰኔ 2026 መንግስት ውድድሮቹ የሚዘጋጁበትን አዲስ ደንብ ለማስተካከል እስኪሰራ ድረስ በመላ ሀገሪቱ የሚደረጉ እንዲህ ያሉ ውድድሮችን አግዳል፤​በወቅቱ ሀገሪቱ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣት ሴቶችን ለመሸለም እና ብዙ ልጃገረዶችን በሳይንስ መስክ እንዲሰማሩ ለማበረታታት ታስቦ የተዘጋጀውን ሃኪሊ ሙሶ የተባለውን ብሔራዊ የሳይንስ ውድድር አስተዋውቃለች። በመስከረም 2026 የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ውድድር በሂሳብ፣ በፊዚክስ እና በኬሚስትሪ የተወዳደሩ 84 ወጣት ሴቶችን አሰባስቧል።ሸናፊዎቹ የገንዘብ ሽልማቶችን፣ ሞተር ሳይክሎችን፣ ላፕቶፖችን እና ነፃ የትምህርት ዕድሎችን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶችን ተቀብለዋል። ውድድሩ ሳይንስ ለወንዶች ብቻ የተወሰነ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ለመለወጥ እና ተጨማሪ ልጃገረዶች የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ የሙያ መስኮችን እንዲመረምሩ ለማበረታታት ያለመ ነው። በጥቅምት ወር ላይ ደግሞ የሀገሪቱ የባህል ሚኒስቴር የቡርኪና ፋሶን ባህል እና ሀገር በቀል እሴቶችን ለማስተዋወቅ ማቀዱን ተናግሯል።