← All news
News Oct 15, 2026 · 23d ago

በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ዛሬ በድሮን የታገዙ ውጊያዎች መደረጋቸዉ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ የፌደራል ጦርና የትግራይ የሰላም ኃይል ተዋጊዎች ከህወሓት ኃይል ጋር በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ዛሬ በድሮን የታገዙ ውጊያዎች ማድረጋቸዉ ተነግሯል። አንድ የትግራይ የሠላም ኃይል አዛዥ በተለይ ለዶቸ እንደተናገሩት የፌደራለ ሰራዊትና የትግራይ የሰላም ኃይል በጋራ በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ተምቤን ልዩ ስሙ ሸውዓተ አሕጉምና አበርገለ በተባሉ አካባቢዎችውግያ እየተካሄደ ነዉ።እኒሁ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ተዋጊ ጦርነቱ በድሮን የታገዘ እንደሆነ ገልጸዋል። አሁን እየተካሄደ ያለው ውግያ «ከአለፈው ጦርነት የተረፉ የህወሓት ሰራዊት አባላት ከአካባቢው ለማፅዳት ነው» ብለዋል።በተጨማሪም የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ከሆነችው ራማ ከተማ ከመረብ ወንዝ 2 ኪሎሜትር ርቆ በሚገኝ ስፍራ ጨው በተባለ ቦታ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአካባቢው በነበሩ የኤርትራ ጦር  የከባድ መሳሪያዎች በድሮን መደብደቡን አዛዡ አስታዉቀዋል። Via DW