← All news
News Oct 15, 2026 · 23d ago

“በቀይ ባሕር የሚደቀኑ አደጋዎችን ከኢትዮጵያ

በላይ  የሚመክት ጠንካራ ኃይል  የለም" የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ፣ የ130 ሚሊዮን ሕዝብን ዕድገትና ፍላጎት ማሟላት የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ያስፈልገኛል ማለቷ የሕልውና እንጂ የምርጫ ጉዳይ ብቻ አይደለም ብለዋል። በቀይ ባሕር እና አካባቢው የሚከሰቱ የደኅንነት ስጋቶችን ከኢትዮጵያ በላይ በባለቤትነት የሚከላከል ኃይል እንደሌለ ገልጸው፣ በውሃ አካላት ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ቀውስ የሀገሪቱን ደኅንነትና ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑን አስረድተዋል። ዋና አዛዡ አክለውም፣ ኢትዮጵያ ለራሷም ሆነ ለቀጣናው ሰላም ዋስትና የመሆን ታሪካዊ ኃላፊነት እንዳለባት አጽንኦት ሰጥተዋል። የባሕር ኃይሉን አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማጠናከር የህልውና ጉዳይ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አካባቢ አዎንታዊ ሚና የምትጫወትበት ጊዜ እጅግ እየቀረበ መምጣቱን ተናግረዋል።