← All news
News Oct 15, 2026 · 23d ago

በኢትዮጵያ ከ 100 የኢንተርኔት ተጠቃሚወች ዉስጥ 67  የካርድ ዋጋ መወደድ ተግዳሮት ሁኖባቸዋል ተባለ

ማህበራዊ ሚዲያን ለጥሩ ነገር ለመጠቀም ከሚያጋጥሙ ዋነኛ ምክንያቶች መካከል የኢንተርኔት ካርድ መወደድ አንዱ መሆኑ ተገልጿል። የስልክና የኮምፒውተር እጥረት፤ 38 በመቶ እንዲሁም የዲጂታል እውቀት ማነስ ፤38 በመቶ ሰዎችን የሚፈታተኑ መሆናቸው የፓሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ባዘጋጀው መድረክ አዲስ የምርምር ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። ይህን የማህበራዊ ሚዲያ ሱሰኝነት እና አላግባብ አጠቃቀም ለመቀነስ ከ100 ሰዎች 64ቱ በህግ ጥብቅ ቅጣት እንዲጣል የሚደግፉ ነዉ ተብሏል ። የማህበራዊ ሚዲያ ሱሰኝነት እና ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ ላይ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን ተነግሯል። ከ100 ተጠቃሚዎች ውስጥ 35 የሚሆኑት የጥላቻ ንግግሮች የሚያሰራጩ ሲሆን፣ 28 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የብሄር እና የሃይማኖት ግጭት ፈጣሪ መረጃዎች ይደርሷቸዋል ተብሏል። 65 የሚሆኑት ደግሞ በሃይማኖት፣ በባህል እና በማህበረሰብ እሴቶች ላይ የተመሰረተ ትምህርት መስጠት መፍትሔ ይሆናል ተብሎ ተቀምጧል። ህዝቡ ከሱሰኝነትና ከስነ-ልቦናዊ አደጋዎች እንዲጠበቅ መንግስት የህግ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ፣ አደገኛ ይዘቶችን የሚቆጣጠሩ አሰራሮችን እንዲዘረጋ እና ህዝቡን የሚያነቁ የትምህርት ፕሮግራሞችን በፍጥነት እንዲጀምር  በመድረኩ አሳስቧል። ኢትዮ ኤፍ ኤም