የአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ብልሽት ተስተካክሎ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ተመለሰ
በአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ አጋጥሞ በነበረ የትራንስፎርመር ብልሽት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች ባደረጉት ርብርብ ዛሬ ረፋድ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት መመለሱ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቴክኒክ ባለሙያዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት የተበላሸውን ትራንስፎርመር በሌላ በመተካት የኃይል አቅርቦቱን ወደ ነበረበት መመለስ ተችሏል። በትራንስፎርመር ብልሽቱ ምክንያት ከማከፋፈያ ጣቢያው ወጪ የሚሆኑ 12 የመካከለኛ መስመር ፊደሮች ተቋርጠው ቆይተው እንደነበርና፣ በዚህም ሳቢያ በተወሰኑ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ኃይል በጊዜያዊነት በማባደር ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት ጥገናው ተጠናቆ ኃይል ያገኙ አካባቢዎች፡- አካባቢ 1፡ ሉካንዳ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምፕርሄንሲቭ ት/ቤት፣ አባጃሌ፣ ኮልፌ 18፣ ኮልፌ መናፈሻ፣ አጠና ተራ፣ ታይዋን፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ በከፊል፣ ሎሚ ሜዳ፣ እና ኢንዱስትሪ መንደር። አካባቢ 2፡ አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን አካባቢ፣ እህል በረንዳ፣ ማሳለሚያ፣ አውቶብስ ተራ፣ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፣ ሻንቅላ ወንዝ፣ ኳስ ሜዳ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ሰፈረ ሰላም፣ ግሩም ሆስፒታል፣ አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ እንዲሁም ድሬ ህንጻ ፊት ለፊት። አካባቢ 3፡ ጦርኃይሎች፣ ቀራንዮ፣ ቤተል፣ መንዲዳ፣ አውጉስታ፣ ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕና አካባቢዎቻቸው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በወቅቱ በነበረው መስተጓጎል ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፤ ደንበኞች ችግሩን ተረድተው ላሳዩት ቀና ትብብርና ትዕግስት ላቀ ምስጋና አቅርቧል። በተጨማሪም የኃይል አቅርቦቱ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ቀንና ሌሊት ላለፉት የሁለቱ ተቋማት ባለሙያዎች ከፍተኛ ምስጋና ተቸሯቸዋል። ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም