← All news
News Oct 15, 2026 · 24d ago

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኡጋንዳ ላይ ጥላው የነበረውን የቪዛ ገደብ አነሳች

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) በኡጋንዳ ላይ ጥላው የነበረውን የቪዛ እገዳ እና የጉዞ ክልከላ ስታነሳ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በደቡብ ሱዳን ላይ የተጣለው እገዳ  እንደሚቀጥል አስታውቃለች፡፡   ሀገሪቱ ቀደም ሲል የኢቦላን   ወረርሽኝ ተከትሎ በኡጋንዳ፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ደቡብ ሱዳን ላይ የቪዛ ገደብ ጥላ የነበር ሲሆን በኡጋንዳ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር መዋሉ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠው የህክምና ክትትል ጊዜ በተሳካ ሁኔታ ማለፉዋን ተከትሎ ገደቡ ሊነሳ ችሏል፡፡   በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በደቡብ ሱዳን ላይ የተጣለውየ ቪዛ ጥያቄ  እና የጉዞ እገዳ እንደሚቀጥል አስታውቃለች፡፡