በጋምቤላ ከተማ ከዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 4፤ 2019 ጀምሮ ከምሽት 12 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ “ላልተወሰነ ጊዜ” የሚቆይ የሰዓት እላፊ ተጣለ። “ለጸጥታ ስራ” ሲባል እንደተጣለ በተገለጸው በዚሁ የሰዓት ገደብ ውስጥ በከተማይቱ የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ “በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን” የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን ይህን እርምጃ የወሰደው፤ በጋምቤላ ከተማ ትላንት ማክሰኞ ምሽት በተፈጸመ ጥቃት ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ነው። ኮሚሽኑ ጥቃቱ የተፈጸመው “ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት” መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ቢያስታውቅም፤ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)