← All news
News Oct 14, 2026 ¡ 24d ago

🚨 «የኤርትራ ሠራዊት አቅምና ከጎረቤት ሀገር ጋር ያለው ወታደራዊ አለመመጣጠን መገለጹ ተመላክቷል»

​የኤርትራ ሠራዊት ከ350,000 በላይ አባላት ያሉት ትልቅ ኃይልን ያሰለፈ ቢሆንም፣ የሚሠሩት 7 አውሮፕላኖች ብቻ እንዳሉት እና አንድም አገልግሎት ላይ ያለ ተዋጊ ጀት (Fighter Jet) እንደሌለው ተገለጸ። ​የወታደራዊ መሣሪያዎች ዕድሜ፦ አብዛኛው የሠራዊቱ መሣሪያ ከ1990ዎቹ የድንበር ጦርነት (1990-1992 ዓ.ም.) ጀምሮ የቆየ መሆኑ ተመላክቷል። ​የመከላከያ በጀት ውስንነት፦ የሀገሪቱ 219 ሚሊዮን ዶላር የመከላከያ በጀት ኤርትራ ከሌሏት ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎች እና ድሮኖች አንፃር ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲወዳደር እጅግ የተገደበ መሆኑ ተገልጿል። ​የቴክኖሎጂ ልዩነት፦ ጎረቤት ሀገራት ኤርትራ በሌሏቸው ድሮኖች እና የጦር መሣሪያዎች እራሳቸውን እያጠናከሩ እና እያመረቱ መምጣታቸው በሁለቱ አካባቢዎች ያለውን የወታደራዊ አቅም ልዩነት እንዳሰፋው ተመላክቷል።