← All news
News Oct 14, 2026 · 25d ago

በአዲስ አበባ ለጠበቆች፣ ገማቾች እና ኢንሹራንስ ወኪሎች አዲስ የግብር መመሪያ ወጣ ‼️

የሂሳብ መዝገብ የሌላቸው ባለሙያዎች 65% ገቢያቸው ላይ ግብር ሊከፍሉ ነው! ይህ ውሳኔ የአገልግሎት ዋጋን ያንረው ይሆን? የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት፦የንግድ ፈቃድ የሌላችሁና የሂሳብ መዝገብ የማታቀርቡ ባለሙያዎች፦ ካገኛችሁት ጠቅላላ ገቢ 35 በመቶው ብቻ እንደ ወጪ ይታሰብላችኋል! የቀረው 65 በመቶው ላይ ግን ሙሉ በሙሉ ግብር እንድትከፍሉ ይደረጋል! ይህ ያልተጠበቀ አሰራር የሚቆየው ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ግን እያንዳንዱ ባለሙያ መደበኛ የሂሳብ መዝገብ ይዞ እንዲሰራ ይገደዳል ተብሏል። ይህ ውሳኔ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ንትርክ አስነስቷል! አንዳንዶች፦ «መንግስት የታክስ ስወራን ለማስቀረት የወሰደው ትክክለኛ እርምጃ ነው» ሲሉ፤ሌሎች ግን፦ «ይህ ውሳኔ ጠበቆችና ባለሙያዎች የአገልግሎት ዋጋቸውን በእጥፍ እንዲጨምሩ ያደርጋል፤ በመጨረሻ የሚጎዳው ተገልጋዩ ተራ ዜጋ ነው!» እያሉ ይከራከራሉ! ይህ አዲሱ የግብር አሰላል ፍትሃዊ ነው ወይስ የዋጋ ንረትን ያባብሳል?