← All news
News Oct 13, 2026 · 25d ago

መከላከያ ሠራዊት፣ ከኤርትራ እና ሱዳን ተልኮ መቀሌ ላይ ማረኳቸው ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ለውጭ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች አሳየ።

የመከላከያ ሠራዊት የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል ተሾመ ገመቹ፣ የውጭ አገራት ወታደራዊ አታሼዎችን ወደ ምድር ኃይል ግቢ ጠርተው የጦር መሳሪያዎቹን ማስጎብኘታቸውን በቦታው ነበርኩ ያሉ አንድ ምንጭ ነግረውናል።ጀኔራሉ፣ የሱዳንና ኤርትራ መንግሥታት ለሕወሃት የላኳቸው ናቸው ያሏቸው ድሮኖች ጭምር ትግራይ ውስጥ መገኘታቸውን ተናግረዋል ተብሏል።በሠራዊቱ እጅ ገብተዋል የተባሉትን ድሮኖች በቢሾፍቱ አየር ኃይል ግቢ በመጪው ሐሙስ ለማሳየት ቀጠሮ እንደተያዘ ጨምረው ምንጩ ገልጸዋል። Via Wazema