የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን
በእስራኤል እንዳያርፍ ተከለከለ እሁድ ሌሊት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ቴል አቪቭ የደረሰው የካርጎ አውሮፕላን ፓይለቱ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሌላት ኢንዶኔዥያ ዜጋ መሆኑ በመታወቁ እንዳያርፍ ተከልክሏል። የሠራተኞች ዝርዝር አውሮፕላኑ ከተነሳ በኋላ በመላኩ አውሮፕላኑ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጎ ኢንዶኔዥያዊው ፓይለት በሌላ አብራሪ ቀይሮ ተመልሶ እስራኤል መግባቱ ታውቋል። ክስተቱ በቅርቡ በፍላይዱባይ አውሮፕላን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል የውጭ አየር መንገዶች የበረራ ደንቦችን ባጠናከረችበት ወቅት የመጣ ነው።