← All news
News Oct 13, 2026 · 26d ago

አዲስ አበባ የንግድ ፈቃድ ለሌላቸው ባለሙያዎች አዲስ የግብር መመሪያ አወጣች‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ ለሚሰሩ እንደ ጠበቆች፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች፣ የኢንሹራንስ ጉዳት ገማቾች እና መሰል ሙያዎች አዲስ የግብር አሰላል ደንብ ተግባራዊ አድርጓል። በዚህ ደንብ መሰረት የሂሳብ መዝገብ የማያቀርቡ ባለሙያዎች፣ ከጠቅላላ ገቢያቸው 35 በመቶው እንደ ወጪ ታስቦ ቀሪው 65 በመቶ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ተደርጎ ይወሰዳል። መመሪያው ለረጅም ጊዜ የቆየውን ክፍተት ይዘጋል የተባለ ሲሆን፣ አዲሱ ደንብ ግልጽ እና ወጥ የሆነ የምዘና ዘዴ ዘርግቷል ሲሉ የግል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 👉 ይህ አሰራር ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ባለሙያዎች መደበኛ የሂሳብ መዝገብ ይዘው እንዲሰሩ ለማስቻል ቢሮው እርምት ሰጪ እርምጃዎችን እና የቃል ኪዳን ማስገባት ሥነ-ስርዓቶችን ለማስተዋወቅ አቅዷል። አሐዱ ሬዲዮ