← All news
News Oct 13, 2026 · 26d ago

ሌባን ማሰር ወይስ መሾም?.

ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሙስና፣ በሌብነት እና የህዝብን ሀብት በመበዝበዝ የተደረሰባቸው የካቢኔ አባላት አሉ ብለዋል... ይሁንና እነዚህኑ ግለሰቦች መልሶ አምባሳደር እና ዲፕሎማት አድርጎ መሾም ምን ማለት ይሆን?  አንድ ወይም ሁለት ሳይሆን በርካታ ከስልጣን ተነሺዎች በዲፕሎማትነት ወደ ውጪ እንደሚላኩ መረጃዎች ደርሰውኛል፣ አንደኛውማ 'ቻይና ልመደብ ስለሆነ እዛው እንቀጥለዋለን' በማለት ለሀገር ውስጥ እና ለቻይና ባለሀብቶች መናገር ጀምረዋል።  ሌባ ቢሆኑም ዲፕሎማት ተደርገው ቢላኩ ብዙም ብር ስለሌለው አይሰርቁም በሚል ስሌት ይሆን? ሌባ ለአመሉ እንዲሉ መስረቅ የለመደ የኤምባሲዎችን ጣርያ ነቅሎ ሊሸጥ ይችላል።  ከሁሉም በላይ ግን ዲፕሎማትነትን እና ዲፕሎማሲያችንን የሰረቀ የሚላክበት፣ የሚቀጣበት ተደርጎ የሚወሰድበት አግባብ ልክ አይደለም፣ ሀገራቸውን በቅንነት ለሚያገለግሉ ዲፕሎማቶችም fair አይደለም። የሰረቀን ክስ መስርቶ መፋረድ እንጂ በየኤምባሲው ማጨቅ መፍትሄ አይሆንም። ምስጢረስላሴ ታምራት