#እንድታውቁት
የሚዘጋ መንገድ በተመለከተ ከቄራ - በቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ የሚወስደውን መንገድ ለሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች፤ ለቢ.አር.ቲ (BRT) B2 የፈጣን አውቶቢስ መስመር ግንባታ ሲባል ከጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ከቄራ ትራፊክ መብራት በቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው ነባር መንገድ የቀኝ ክፍል ሙሉ በሙሉ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሳውቋል። ከቄራ ንግድ ባንክ ወደ ቀኝ ታጥፎ በቂርቆስ ቤተክርስቲያን በኩል፣ ወይም ከቄራ በሳር ቤት በኩል ወደ አፍሪካ ህብረት የሚወስደውን አማራጭ መንገድ መጠቀም ይቻላል። እንዲሁም ፤ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ የሚወስደው የመንገዱ ክፍል በጊዜያዊነት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት ተደርጓል። ለትራፊክ ፍሰቱ መቀላጠፍ ሲባል በዚህ መስመር ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ ማቆም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስጣን አሳውቋል።