← All news
News Oct 13, 2026 · 26d ago

“ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መብት አላት” — ሶማሊላንድ

ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ዳርቻዎችን እና የበርበራ ወደብን እንድትጠቀም ሁኔታዎችን ለማመቻቸት አሁንም ዝግጁ መሆኗን ገለጸች። የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዲራህማን ዳሂር ባካል እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት የምትችል ረጅም የባሕር ዳርቻ አለን፤ በተጨማሪም የበርበራ ወደብ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚደርሰው አቅሙ እስካሁን ጥቅም ላይ አልዋለም ብለዋል። ሚንስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ከሚጥስ ማንኛውም ኃይል ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ገልጸዋል። አያይዘውም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ውዝግብ በንግግር እንዲፈታ ጥሪ ማድረጋቸውን ስካይ ኒውስ ዓረቢያ ዘግቧል።