← All news
News Oct 12, 2026 · 27d ago

የኤርትራ ሰራዊት እየወጣ ነው‼️

ከዛላምበሳ እስከ ራማ፤ የኤርትራ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ግዛት እየወጡ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል። የኤርትራ ኃይሎች ይዘዋቸው የነበሩትን የትግራይ አካባቢዎች ለቀው፣ ወደ ራሳቸው ግዛትና ምሽጎች እየተመለሱ መሆናቸውን የመረጃ ምንጫችን አስታውቋል። ምንጫችን እንደገለጸልን፣ ይህ ማፈግፈግ በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፣ ዛላምበሳን፣ ራማንና ሌሎች ይዘዋቸው የነበሩ አካባቢዎችን የሚያካትት ነው። ከምስራቅ ትግራይ * ኣዘባ * ሙጉላት * ክሳድ ዓሌቛ * ፋፂ 📌 ሰሜን ምዕራብ ትግራይ * ሸመልባ * ዓዲ ሃገራይ፣ * ዛግርን * ዓዲ ኣዋዓላን * ሽራሮ  የኤርትራ ኃይሎቹ እነዚህን ቦታዎች ለቀው ወደ ኤርትራ ግዛት መመለሳቸውን ተጠቅሷል። ከዚህ በተጨማሪ ሀብት የጫኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖች በራማ ወደ ኤርትራ እየተሻገሩ መሆኑ ታውቋል። ትናንት ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም በዛላንበሳ በኤርትራ ሰራዊት ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከባድ ጉዳት አስተናግዷል ተብሏል።