ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን እየተከበረ ነው
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት መከበር ጀምሯል፡፡ “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ መከበር የጀመረውን የሠንደቅ ዓላማ ቀን ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አስጀምረዋል። ሁነቱ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስተባባሪነት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች በተመሳሳይ ሰዓት እየተከበረ ይገኛል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አህመድ ሺዴ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተገኝተዋል።