← All news
News Oct 12, 2026 · 27d ago

አቢሲኒያ ባንክ የአጠቃላይ ተቀማጭ ሀብት መጠኑ 381 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገለጸ

ባንኩ እ.ኤ.አ በ2025/26 በጀት ዓመት የ11 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ የአቢሲኒያ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መኮንን ማንያዘዋል በባንኩ 30ኛ መደበኛ እና 17ኛው አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤው ላይ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ ውስጥ 55 ነጥብ 24 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ መኮንን ገለጻ የባንኩ አጠቃላይ ገቢ 55 ነጥብ 24 ቢሊየን ብር ሲደርስ ትርፉ ካለፈው ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ10 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ16 ነጥብ 17 ቢሊዮን ብር ብልጫ በማሳየት 55 ነጥብ 24 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል። የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 318 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር መድረሱ ሲገለጽ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ደግሞ 381 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ደርሷል ተብሏል፡፡