← All news
News Oct 11, 2026 · 27d ago

የዩጋንዳው ጄኔራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ ለጌታቸው ረዳ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላለፉ

የዩጋንዳ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ጄኔራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ዳግም መሾማቸውን ተከትሎ የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጄኔራሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በኤክስ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራውን የሹመት መረጃ በድጋሚ በማጋራት፣ «እንኳን ደስ አለህ ወንድሜ!» የሚል መልዕክት ጽፈዋል።