በሽሬ ከተማ የህወሓት መሣሪያ ማከማቻዎች በሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ዋለ
በሽሬ ከተማ ለረጅም ጊዜ ተደብቀው የቆዩ የህወሓት ቡድን መሣሪያ ማከማቻዎች በሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮች አስታውቀዋል። በማከማቻዎቹ ውስጥ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፣ ተተኳሾች፣ የመሣሪያ መለዋወጫዎችና ወታደራዊ ትጥቆች እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ያሳያል። በሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር ከዋሉት ቁሳቁሶች መካከል የ120 ሚሊሜትር ሞርተር፣ የቢኤም እና የኤግላ መሣሪያዎች፣ የእስትሬላ፣ ዙ-23፣ ክላሽ፣ ድሽቃ፣ መትረየስና የታንክ ተተኳሾች እንዲሁም የእጅ ቦንቦች እንደሚገኙበት ተገልጿል። የተገኙት የመሣሪያ መለዋወጫዎችና ወታደራዊ ትጥቆችም በሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። በተያያዘ ዜና፣ በሽሬና በአካባቢው የሕወሓት አባላት እንደሆኑ የተገለጹ ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን ትተው እጃቸውን እየሰጡ ነው።