← All news
News Oct 11, 2026 · 28d ago

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል። የአየር መንገዱ አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ መቀሌ ከተማ አርፏል። ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በረራ መጀመሩን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደስታቸውን እየገለጹ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።