← All news
News Aug 26, 2026 · 13d ago

ለአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርት ሊሰጥ ነው

​በመጪው የ2019 ትምህርት ዘመን በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርት ለመስጠት የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ​በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ መሪ አስፈፃሚ ዶ/ር ዮሀንስ ወጋሶ እንዳስታወቁት፣ ዕቅዱ ተማሪዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ ለማድረግ እና የውጭ ሀገር የከፍተኛ ትምህርት እድሎችን እንዲጠቀሙ ለማስቻል ያለመ ነው። ትምህርቱን የሚያስተምሩ መምህራንም ከቻይና መንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገልጸዋል። ​አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ በመለያ ፈተና ያለፉ ከፍተኛ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች የሚያስተናግዱ ሲሆን፣ በቀጣይም ከቻይንኛ በተጨማሪ ሌሎች አለምአቀፍ ቋንቋዎች ተጠናክረው እንደሚሰጡ ተጠቅሷል። በአንፃሩ ቻይና በአሁኑ ወቅት አማርኛን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ቋንቋዎችን በሀገሯ በስፋት እያስተማረች ትገኛለች።