← All news
News Aug 25, 2026 · 13d ago

#NGAT_Protocols

የ2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከነገ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጠዋት እና በከሰዓት ፈረቃ ይሰጣል። ➫ ተፈታኞች ፈተናው ከሚጀመርበት 3ዐ ደቂቃ ቀድመው በመፈተኛ ማዕከል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ➫ ፕሪንት ያደረጉትን የመፈተኛ መግቢያ ትኬትዎን (Entrance Ticket) መያዝ አይዘንጉ። ➫ ተፈታኞች ከተመደቡበት ማዕከል ውጪ መፈተን አይችሉም። ➫ የብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ የግድ መያዝ ይኖርብዎታል፡፡ ➫ የሞባይል ስልክ፣ ሚሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት፣ ... የመሳሰሉ ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች ይዞ ወደ ፈተና ማዕከል መሔድ አይቻልም።