← All news
News Aug 25, 2026 · 13d ago

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል። ውጤት ለማየት ፦ 👉 በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et 👉 ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram 👉 አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ገልጿል።