"አለሁ አልሞትኩም!" አቶ እስክንድር ነጋ
እረስክንድር በቅርቡ "ሞቷል" ተብሎ የሚናፈሰውን መረጃ ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል። ባለፉት 4 ዓመታት በተደጋጋሚ ከመሬትም ከአየርም (በድሮን) የታለሙ የግድያ ሙከራዎች እንደተደረጉበትም ለዶቸቬለ ገልጿዋል። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ያላሰለሰ እንቅስቃሴና ጥቃት ግልጽ ቢሆንም፣ ስለሌሎች የታጠቁ አካላት እጅ ግን ለጊዜው አስተያየት መስጠት እንደማይፈልግና በሂደት የሚታወቅ እንደሆነ ተናግሯል። የፋኖ ትግል ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ ረጅም እጆችና የጎጠኝነት አስተሳሰቦች ገብተውበት እንደነበርና ይህም በአመራርነት ለመቀጠል አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሮ እንደነበር ተናግሯል። የፋኖና የሌሎች አማፂያን ጥምረት የተቋቋመው በጊዜያዊ ሽግግር አመራርና በምደባ እንደነበር ጠቅሷል።ደም እየፈሰሰ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ማንኛውም ውሳኔና ድርድር የአባላትንና የህዝብን ቀጥተኛ ተሳትፎና ውሳኔ ማካተት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።