የገዱ አንዳርጋቸው ንጹህ እንጀራ ።
ከመሸ ፌስቡክ ላይ የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ኋላ ላይም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፡ በሀገረ አሜሪካን የፓርኪንግ ስራ ሲሰሩ የሚያሳይ ቪዲዮ አየሁ ። ........ አደለም የአንድ ክልል ፕሬዝደንት ፡ አደለም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረ ሰው ይቅርና ፡ ተራ የገቢዎችና ጉምሩክ ሰራተኛ እንዲሁም በተለያየ የመንግስት ቢሮዎች ያሉ ሃላፊዎች ዱባይ ውስጥ ቪላ በሚገዙበት ዘመን ። ተራ ባለስልጣን በዘመድ አዝማዱ ስም ሚሊዮኖችን በባንክ በሚያስቀምጥበት ጊዜ ፡ የሀገርን ሀብት በውጭ ባንኮች የሚያስቀምጡ እልፍ ባለስልጣኖች ባየንበት ዘመን ፡ ልጆቻቸውን በአውሮፓና አሜሪካ የሚያስተምሩ ሙሰኞች በሞሉበት ጊዜ ፡ ደጉ አንዳርጋቸው የሚባል ሰው ፓርኪንግ እየሰራ ይገኛል ሲባል የማይገረም ማን ይኖራል ? ..... አቶ ገዱ ስለሚያራምደው ፓለቲካዊ አመለካከትም ሆነ ሌላ ነገር ግድ የለኝም ። በስልጣን በነበረበት ጊዜ ከዚች ድሀ ሀገር ሳይዘርፍ በመኖሩ ግን በአክብሮት እጅ ለመንሳት እገደዳለሁ ። ማንም ሰው ይህን አለማድነቅ አይችልም ። አቶ ገዱ ቢፈልግኮ ይህኔ በአሜሪካን ባንኮች መቶ ሚሊዮኖችን ማስቀመጥ ይችል ነበር ። ሆኖም አላደረገውምና ዛሬ ላይ ፓርኪንግ ተቀጥሮ እየሰራ የሰላም እንቅልፍ ተኝቶ ያድራል ። .... የገዱ ንፁህ እንጀራ ያስቀናል ፡ በሙስና ያልቆሸሸ ፡ ከድሃ ሀገር ከተዘረፈ ገንዘብ ጋር ያልተነካካ ንፁህ እንጀራ ።