የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 125 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ሊሸጥ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቡዕ፣ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሚያካሂደው የ27ኛው ዙር የውጭ ሀገር ገንዘብ (FX) ጨረታ ይፋ አድርጓል። በዚህ ጨረታ ላይ 125 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው ባንኮች የተዘጋጀውን መመሪያ ተከተለው እንዲወዳደሩ ተጠይቀዋል። የጨረታ ሰዓት: ከጠዋቱ 4:00 እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት የማስገቢያ መንገድ: በCSD ኤሌክትሮኒክ የሐራጅ ሥርዓት በኢሜይል ውጤት የሚገለጽበት: በዕለቱ ከሰዓት በ9:00 ሰዓት ክፍያና ሂሳብ ማጣሪያ : ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የሥራ ቀን ማጠቃለያ ላይ ይፈጸማል።