1,501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል ነገ ማክሰኞ በመላው ሀገራችን እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።
የዘንድሮው በዓል የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮን መሠረት በማድረግ " የፍትሃዊው ነብይ " በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ መርሐ-ግብሮች ይከበራል። መውሊድ በሀገርአቀፍ ደረጃ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ሆኖ ከሚከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነው።