← All news
News Aug 24, 2026 · 15d ago

ትራምፕ ካናዳ የአሜሪካ ክፍለ ሀገር ሳትሆን የክፍለ ሀገርነት ጥቅሞችን ትፈልጋለች ሲሉ ወቀሱ

👉በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ውጥረት ተባብሷል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ ዕለት በካናዳ ላይ ጠንካራ ወቀሳ ያቀረቡ ሲሆን፤ ሀገሪቱ የአሜሪካ ክፍለ ሀገር ሳትሆን የክፍለ ሀገርነት ጥቅሞችን ትፈልጋለች ብለዋል። ይህ አስተያየት የተሰጠው የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ የተሰናከለውን የንግድ ድርድር ተከተሎ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የአጸፋ ታሪፍ እንደሚጣሉ ካስታወቁ በኋላ ነው። የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ በሁለቱ የቆዩ ወዳጆች መካከል የተፈጠረው ክፍተት እየሰፋ በሄደበት ወቅት ከመጥፎ የንግድ ስምምነት ራሳቸውን ማግለላቸውን ገልጸው ቅዳሜ ዕለት በአሜሪካ ላይ የአጸፋ ታሪፍ መጣላቸውን ይፋ አድርገዋል። በጎረቤታሞቹ ሀገራት መካከል በዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረው ድርድር አርብ ዕለት ተቋርጧል።   ይህም 20 ቢሊዮን ዶላር ግምት ባላቸው እና ወደ አሜሪካ ከሚላኩ የካናዳ ምርቶች ውስጥ 5.5 በመቶ ድርሻን በያዙ የካናዳ ዕቃዎች ላይ አዲሱ  የአሜሪካ  50 በመቶ ታሪፍ ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል። ታሪፉ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ከሆኪ እንጨት እስከ ሲሚንቶ ይገኙበታል። ጥቃት ሲሰነዘርብህ በጦርነት ውስጥ ነህ ማለት ነው። እኛም ጥቃት ተሰንዝሮብናልሲሉ ካርኒ ተናግረዋል። ትራምፕ በማህበራዊ ገጻቸው ትሩዝ ሶሻል ላይ ባሰፈሩት መልእክት፥ ለብዙ ዓመታት በታላላቅ ገበሬዎቻችን ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ሲያስከፍሉ ቆይተዋል። ከእንግዲህ ይህ ይበቃል ብለዋል።