← All news
News Aug 23, 2026 · 15d ago

#NGAT

የሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket አሁን ላይ ማግኘት እንደምትችሉ ተገልጿል። በመሆኑም ፕሮፋይላችሁ ላይ በመግባት 'Exam Credentials' በሚለው ስር 'Download Entry Ticket' የሚለውን በመጫን ወደ ፈተና ማዕከል መግቢያ ትኬትዎን አውርደው ፕሪንት ያድርጉ። ፈተናው ከሚጀመርበት ሰዓት 30 ደቂቃ ቀድማችሁ መድረስ ይጠበቅባችኋል።  ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡