የገቢዎች ቢሮ በኮሚሽን ነጋዴዎች ግቢ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች በአስቸኳይ እንዲነሱ አዘዘ
የገቢዎች ቢሮ በኮሚሽን ነጋዴዎች ግቢ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች በአስቸኳይ እንዲነሱ አዘዘ የአዲስ አበበ ገቢዎች ቢሮ በተሽከርካሪ ኮሚሽንና አገናኝነት ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የሻጮችን ተሽከርካሪ በድርጅታቸው ቅጥር ግቢ አከማችተው መሸጥ በህግ የተከለከለ መሆኑን በመግለጽ፣ በግቢያቸው የሚገኙ መኪኖችን በአስቸኳይ እንዲያነሱ ጥብቅ ትእዛዝና ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። ቢሮዉ ያስተላለፈውን ጥብቅ መመሪያ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አብዛኞቹ የኮሚሽን ነጋዴዎች ተሽከርካሪዎችን ከግቢያቸው እያወጡ ይገኛሉ።