← All news
News Aug 22, 2026 · 17d ago

የትራምፕ ቪዛ እገዳ በፍርድ ቤት ተሻረ

የኒውዮርክ የፌደራል ፍርድ ቤት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ75 ሀገራት በሚመጡ ዜጎች ላይ ጥሎት የነበረውን የኢሚግሬሽን ቪዛ እገዳ ውድቅ አደረገ። ​የፍርድ ቤቱ ዳኛ ጄኔት ቫርጋስ በሰጡት ውሳኔ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያሳለፈው ይህ እገዳ "በግልጽ ህገ-ወጥ" እና ከሚኒስቴሩ ህጋዊ ስልጣን ውጭ ነው ብለዋል። ውሳኔው በዜግነት ላይ የተመሰረተ መድልዎ በመሆኑ ከሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ህግ ጋር እንደሚጋጭም ገልጸዋል። ​እገዳው ከአፍሪካ፣ ከላቲን አሜሪካ፣ ከእስያ እና ከአውሮፓ የመጡ የቪዛ አመልካቾችን የጎዳ ሲሆን፣ የትራምፕ አስተዳደር አመልካቾቹ "በመንግስት ላይ ጥገኛ የመሆን ስጋት አለባቸው" የሚል ምክንያት አቅርቦ ነበር። ​ክሱን የመሰረቱት የኢሚግሬሽን መብት ተሟጋች ድርጅቶች በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መደሰታቸውን ሲገልጹ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። ዘገባው የአልጀዚራ ነው