← All news
News Aug 21, 2026 · 17d ago

ነገ ቅዳሜ በመቀሌ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የአሽንዳ ዓመታዊ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሠረዘ።

የአሸንዳ በዓል ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት የተሠረዘው፣ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄደው የድሮን ጥቃት ሳቢያ መኾኑን የትግራይ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጧል። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አንቂዎች፣ በክልሉ በሴቶች ላይ የሚፈጸመሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በመቃወም ሴቶች በዓሉን ጥቁር በመልበስና "ጥቁር አሸንዳ" በሚል መሪ ቃል እንዲያከብሩት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ፣ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ከመደበኛው ባሕላዊ ስነ ሥርዓት ውጪ ሌላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም ሲል ሰሞኑን ማስጠንቀቂያ አውጥቶ እንደነበር አይዘነጋም።