← All news
News Aug 21, 2026 · 17d ago

ኢትዮጵያ ግብፅ የጀመረችዉን ዘመቻ አጥብቃ ተቃወመች

ኢትዮጵያ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በዓባይ ወንዝ ልማት ላይ ያላትን አቋም ለማዛባት ግብፅ በድጋሚ የጀመረችውን ዘመቻ አጥብቃ መቃወሟን የተለያዩ የዉጭ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። መገናኛ ብዙሃኑ ይፋእንዳደረጉት ኢትዮጵያ  የዓባይ ወንዝን የመጠቀም መብቷ፤ በሉዓላዊ የልማት መብት እና ለክልሉ የጋራ ተጠቃሚነት ባላት ዓላማ ላይ የተመሰረተ መሆኑን መንግስት አስታውቋል። በአፍሪቃ ረጅሙ ወንዝ  ዓባይ፣ በ 11 ሀገራትን አቋርጦ በግብፅ በኩል ወደ ሜዲትራኒያን ባህር የሚቀላቀል ነው። በዚህ ወንዝ ላይ በሚገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል  አለመግባባት በመፍጠር ውዝግቡ ከአስር ዓመታት በላይ ዘልቋል። የኢትዮጵያዉ የሕዳሴ ግድብ  የሚገኘው የግድቡ ግንባታ በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ  2011 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፣ በይፋ የተመረቀው ደግሞ በጎርጎሪያኑ መስከረም 2025 መሆኑ ይታወሳል።