← All news
News Aug 20, 2026 · 18d ago

ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ 14 አመት ሆኗቸዋል

ከ 14 አመታት በፊት ነሃሴ 14 ቀን የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስትር እና የህወሓት ሊቀመንበር የነበሩት መለስ ዜናዊ አስረስ ከዚህ አለም በሞት የተለዩበት እለት ነዉ። ጠ/ሚኒስትር መለስ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሁለት አይነት አመለካከት ያላቸዉ ሲሆን ግማሾች ባለራዕይ ፣ ቆራጥ እና ጀግና መሪ ሲሏቸዉ ግማሾች ኢትዮጵያን የብሔር ፖለቲካ ዉስጥ የከተቱ ፣ ከፋፋይ መሪ ይሏቸዋል። በጠ/ሚኒስትር መለስ አገዛዝ ዘመን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ያሳየችበት ፣ የአባይ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት እንዲሁም በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የተከፈቱበት እና ከቀደመዉ አገዛዝ ለዉጥ የታየበት ነዉ ሲሉ በርካቶች ግን ኢትዮጵያዊ ዛሬ ላይ ጭምር ላለችበት የብሔር ግጭት መሰረት የጣሉ ሰዉ ናቸዉ ይሏቸዋል። ጠ/ሚኒስትር መለስ በ 2002 ዓ.ም ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት። ጠ/ሚኒስትሩ ለ 2 ወራት በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ  ህይወታቸው ማለፉን በወቅቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መዘገቡ አይዘነጋም። ጠ/ሚኒሰትሩ በሌሊት በቤልጂየም ነሃሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር በ 57 አመታቸዉ ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት።