← All news
News Aug 20, 2026 · 19d ago

በመቀሌ ከተማ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ 13 ሰዎች ቆስለው አይደር ሆስፒታል ገቡ።

የመጀመሪያው ጥቃት በሐወልቲ ክፍለ ከተማ፣ ሞሞና ቀበሌ፣ በቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አቅራቢያ የመኖሪያ ቤቶችን ኢላማ ያደረገ ነበር ተብሏል። አይደር ሆስፒታል እንዳስታወቀው፤ ዛሬ ጠዋት 5:30 ገደማ አዋቂዎችንና ህፃናትን ያካተቱ 13 ተጎጂዎችን ተቀብሎ አስቸኳይ ቀዶ ህክምና እያደረገላቸው ይገኛል። ሁለተኛው ጥቃት ደግሞ በመቀሌ ኩሃ አካባቢ መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል። በጥቃቱ ስለደረሰው የንብረትና የሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃዎች እየወጡ ነው። መቀሌ አሁንም በከፍተኛ ስጋት ላይ ትገኛለች።